News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
መጋቢት 20/2017 ዓ.ም.
# ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ
የ2024-25 የስራ ክንውን እና የኦዲት ሪፖርት የቀረበ ሲሁን፣ ጉባዔው ሪፖርትና አዲቱን ካደመጠ በኋላ የተለያዩ ሀሳቦችን አንስቶ ውሳኔ አሳልፏል። የግሎባል ፒስ ባንክ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ፣ ለጉባዔተኞቹ በዓመቱ የተሰሩትን ዝርዝር ተግባራት ያቀረቡ ሲሆን፣ በዚህም መሰረት ከማህበሩ ዓላማ አንስቶ እስከዕቅድና አፈፃፀም ድረስ የነበሩትን ሂደቶች አብራርተዋል።
የረጅምና አጭር ጊዜ ዕቅዶች፣ በትግራይ ክልል ስለተደረጉ የተፈናቃይና በጦርነቱ የተጎዱ የማሕበረ-ሰብ ክፍሎች ጉብኝት፣ ስለጉብኝቱ ተሳታፊያን፣ከመንግስትና ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር ስለተደረጉ ውይይቶች፣ በተጨማሪም፣ ከጊዚያዊ መንግስቱ ጋር ስለተደረጉ ምክክርና መግባቢያዎች፣ ስለተደረጉ እርዳታዎች በሪፖርቱ አቅርበዋል። በሪፖርቱ እንደተመላከተው፣ በጉብኝቱ ወቅት በትግራይ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የመንግስትና የግል ሚዲያዎች ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ስለሰላም ባንኩ መቅረቡን አንስተዋል። የባንኩ አባላት በጉብኝቱ ወቅት የሕዝብ አስተያየት ምልከታ አድርገዋል ያሉት አቶ አርጋው፣ በዚህም አካባቢውንና ማሕበረ-ሰቡ ያለበትን ሁኔታ ተረድተን፣ ከባንኩ አንፃር ምን መሰራት እንደሚገባ ግብዓት ይዘን ተመልሰናል፤ ወደፊት በባንኩ በኩል ስራዎች ይረሳሉ ብለዋል።
በሪፖርት ዓመቱ፣ የድርጅቱ መዋቅር የተሰናዳ ሲሆን፣ አምስት ዋና ዋና የስራ ክፍሎች መዘርጋታቸው ተጠቁማል። ከዚህም ሌላ፣ ከታችኛው የኦሞ ማሕበረ-ሰብ አካላት ጋር ስለተደረሰው አና ስለተጀመረው 'የሰላምና የዕርቅ ማዕከል ግንባታ' የተብራራ ሲሁን፣ አሁን ላይ ስላለበት ደረጃም መረጃ ተሰጥቷል። በጉባዔው እንደተጠቀሰው፣ 497,012.50 ብር የተሰበሰበ ሆኖ፣ 494,700.00 ብር ስራ ላይ ውሏል።
የሰላም ባንኩ ስላጋጠሙ ችግሮችና ስለተወሰዱ የመፍትሄ ስራዎች የተበራራ ሲሆን፣ በበጀት፣ በግዜ፣ በሰው ሀይልና በቁስ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የተለያዩ እርምጃዎችን በመውሰድ እንደተፈቱ ተገልጿል። የተገኙ ጥሩ ተሞክሮዎችን እና ልምዶችን በማስቀጠል፣ የሚፈጠሩ ክፍተቶችን በመሙላት ለተሻለ አፈፃፀም ዕቅድና ተግባር ተጣጥመው እንዲሰሩ በጉባዔው ተሳታፊያን በአፅዕኖት ተመክሯል።
ዝርዝር የበጀት ኦዲት በአቶ ፍሬው ለማ ቀርቦ፣ ለተነሱ ሀሳቦች፣ ጥያቄና አስተያየቶች የባንኩ ስራአስፈፃሚ አካላት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቀረበው የስራና የኦዲት ሪፖርት ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ፣ በአንድ ድምፀ-ተአቅቦ እና በሙሉ ድምፅ ፀድቆ፣ ለግማሽ ቀን የተጠራው ጉባዔ ተጠናቋል።
2025-03-29