News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
--ግንቦት 23 ቀን 2017 ዓ.ም (ግሎባል ፒስ ባንክ ኒውስ)
የሀዋሳዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዲፓርትመንት የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃን ዛሬ በዲፓርትመንቱ መምህራን እና ተማሪዎች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
በሽኝትፕሮግራሙ ላይ በክብር እንግድነት ተጠርተው የተገኙት የግሎባል ፒስ ባንክ ማህበር መሥራች እና ሥራ አስኪያጅ፣ አቶ አርጋው አየለ ለተመራቂዎቹ ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ መልዕክት ግሎባል ፒስ ባንክ ከትምህርት ክፍሉ ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት አውስተው በተለይ ከዚህ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች ጋር የነበራቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ እንደነበር ገልጸዋል።
የትምህርትክፍሉ ተማሪዎች ከአብን ኤዘር ሳፖርቲንግ ኤንድ ደቬሎፕመንት አሶሲዬሽን ሕጻናት ጋር እጅግ በመቀራረብ እና በዓላትን እንደቤተሰብ አብረው በማሳለፍ ጭምር የሚታወቁ ሲሆን ፣በግሎባል ፒስ ባንክ የሰላም ግንባታ ተግባራት ደግሞ የትምህርት ክፍሉ ግንባር ቀደም ተባባሪ መሆኑን አቶ አርጋው ተናግረዋል። ግሎባል ፒስ ባንክ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዲፓርትመንት ጋር ሲያካሄድ የነበረውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እና ተቋማዊ ለማድረግ በመወሰን በቅርቡ የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ያስታወሱት አቶ አርጋው የዚህ ዓመት የትምህርት ክፍሉ ምሩቃን በእየሄዱበት ሁሉ የግሎባል ፒስ ባንክ አምባሳደር እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በሽኝትፕሮግራሙ ላይ ከአቶ አርጋው አየለ ጋር የተገኙት የግሎባል ፒስ ባንክ የሰላም ግንባታ እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር፣ አቶ ዳያሞ ዳሌ በበኩላቸው ከዚህ ዓመት ምሩቃን ጋር ባላቸው ትውውቅ እንደሚኮሩ ገልጸው የምሩቃኑን ሞያዊ ብቃት እና ችሎታ አድንቀዋል። የዚህ ዓመት ምሩቃን የተማሪነት ዘመናቸውን ጨርሰው ወደ ህብረተሰብ የሚቀላቀሉበት ወቅት የአገራችን ማህበረሰብ የሀሳብ ልዩነቶችን በማስተናገድ የመቻቻል ባህልን ማዳበር በሚያስፈልገው ወቅት መሆኑን የጠቀሱት አቶ ዳያሞ ምሩቃን በሰለጠኑበት ሞያ እና ባዳበሩት ሥነምግባር ለማህበረሰባችን የመቻቻል እና የሰላም ባህል ግንባታ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
በፕሮግራሙላይ የጋዜጠኝነት እና ኮሚዩኒኬሽን ተማሪዎች ማህበር ተወካዮች አቶ አርጋው አየለ ለማህበሩ ስላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነው የምስክር ወረቀት እና ሽልማት አበርክተውላቸዋል።
2025-06-01