News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
ግሎባልፒስ ባንክ ፣ "በአፊኒ ሶንጎ" የመድርክ ተውኔት ዝግጅት ላይ ውይይት አካሄደ። በሲዳማ ባህላዊ ግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ ያተኮረ የመድረክ ተውኔት ለማዘጋጀት በተካሄደው የግብዓት ማሰባሰብ አና የውይይት መድረክ፣ ከሲዳማ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት፣ ከክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ ከክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ እና ግሎባል ፒስ ባንክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት መሰረት ወደትግበራ የተገባ ሲሆን፣ የድራማው የመጀመሪያ ደረጃ ስራ ምክረ-ሐሳብ ዝርዝር እቅድ፣ የግዜና የበጀት አዘገጃጀትን ያካተተ ሰነድ ቀርቧል።
በመድረኩየተገኙት የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የባህል ዘርፍ ኃላፊ፣ ክቡር አቶ ዳዊት ዳንጊሦ፣ በሲዳማ አፊኒ የግጭት አፈታት ሥርዓት ቀደም ሲል የቀረበውን ሲኒማና ያገኘውን ድንቅ ሐገራዊና ዓለማቀፋዊ ተቀባይነት አስታውሰው፣ በተጨማሪም አፊኒ ሶንጎ አዋጅ ተዘጋጅቶለት መደበኛውን የሕግ ስርዓት እንዲያግዝ በቅርቡ በክልሉ ምክር ቤትም፣ ህጋዊ ሰውነት ማግኘቱን አመላክተዋል። ከዚህም ሌላ፣ "በክልላችን የፊልም ኢንደስትሪ ለማቋቋም ጥናት ቀርቦ ወደተግባር ለመግባት ቢሮው ዝግጅት ላይ ነው፤" ያሉት ኃላፊው፣ "አሁንም ይህንን ድራማ በጥልቀት በማየትና በመመርመር ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጁዎች ነን፤" ብለዋል።
የተዘጋጀውንየድራማ አቀራረብ ያሰናዳው፣ ዶ/ር አንዷለም አባተ ( የአጸደ ልጅ) ሲናገር፣ "አፊኒ፣ የህዝቡን የአስተሳሰብ ፈለጎች፣ የማህበረሰቡን ድንቅ ባህሪና ለሰላም ግንባታ ያለውን ትልቅ ግምት አንጸባራቂ ነው፤" ሲል አመላክቷል። ይህንን የግጭት መፍቻ መሣሪያ ታሪክና መቼት አልብሶና አዋቅሮ በማቅረብ ሐገራዊና ዓለማቀፋዊ ገጽታ ለመገንባት መሠረት ሊሆን እንደሚችል፣ ቀደምሲል፣ በሚኤኔት ብሔረሰብ የግጭት አፈታት ሥርዓት ላይ 'ዴጊያ' በሚል ሥርዓት የሰራውን ድራማ ተቀባይነት ያገኘበትን ስልት በመጥቀስ እንደአብነት አቅርቧል።
የግሎባልፒስ ባንክ መሰራችና ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ በበኩላቸው እንደገለፁት፣ "ግሎባል ፒስ ባንክ፣ ሰላምን ለማፅናት ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ፣ ባሕላዊ የግጭት አፈታትን ማስጠናት፣ ማጠናከርና ማጎልበት ሲሆን፣ በድራማ መልክ የሚቀርበው ይህ ስራ ሲጠናቀቅ፣ በክልሉ ከተሞች ለሕዝብ፣ ለተማሪዎችና ለወጣቶች በማሳየት፣ ሰፊው ባሕል ለሰላምና ፍቅር የሚጫወትውን ሚና መስተዋወቅ ነው፤" ብለዋል።
በመድረኩከተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የተገኙ ባለድርሻ አካላት፣ በባሕል፣ ሕግ፣ ኪነጥበብ፣ እና የስነ-ፅሑፍ መምራን ሙያዊ አስተያየት በሰፊው የሰጡ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌዎችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚዲያዎችና ወጣት አንቂዎችም ተገኝተዋል።
በሀዋሳሮሪ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለግማሽ ቀን የተደረገው የምክረ- ሀሳብ መድረክ፣ በቀጣይ ስለሚከናወኑ ስራዎች አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።