News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
በግሎባል ፒስ ባንክ ሪፖረተር
ግሎባል ፒስ ባንክ ከተለያዩ የሚዲያ አገልግሎት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡ “የሚዲያ ሚና ለሰላም ግንባታ” በሚል ርዕሰ-ጉዳይ ላይ ያተኮረው ስልጠና፣ ሰኞ ሀምሌ 14/2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳፋየር ኢንተርናሽናል ሆቴል የተዘጋጀ ሲሆን፣ 22 የሚደርሱ በአገሪቷ ውስጥ የሚሰሩ የራዲዮ፣ የተሌቪዥን፣ በተለያዩ የማሕበራዊ ሚዲያ የሚሰሩና የጋዜጠኞችና ከሚዲያ ማሕበራት የተውጣጡ ባለሙያዎችን ያካተተ ነው፡፡
በስልጠናው መድረክ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የግሎባል ፒስ ባንክ ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ የሚዲያ አካላት በሰላም ግንባታ እና ሀሳብ ዙሪያ ያላቸውን አቅማ አሟጠው በመጠቀም ማሕበረ-ሰቡ፣ ወጣቱና አገር ተረካቢው ትውልድ የተሻለ ዓለም እንዲፈጠርለት ለማስቻል ያለመ ስለመሆን ተናግረዋል፡፡ አክለውም፣ “ከትናንት ቁርሾአችን ወጥትን በሰላም ለመኖር፣ አሮጌ እቃዎችን አዲስ ቤት ለመገንባት እንደማንጠቀመው ሁሉ፣ አገሪቷን በሰላም ረገድ ማሻገር ካስፈለገ፣ በአዳዲስ ሀሳቦች እና እውቀቶች፣ በንግግርና ሰላማዊ ውይይቶች ቅድሚያ ሰጥተን ግጭቶቻችንን መፍታት ቅድሚያ መስጠት ይገባናል፤” ብለዋል፡፡ አክውም፣ የዚህ ዓይነት የስልጠናና ምክክር መድረኮች የሚቀጥሉ ሲሆኑ፣ ከሌሎች የሚዲያ አካላት፣ የኮሙኒኬሽን ተቋማትና በሰላም ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካሆኑ ተቋማት ጋር በሰፊው የሚሰሩ ስራዎች ይሆናሉ ሲሉ አስታውቀዋል፡፡
የመክፈቻው ንግግር ያድረጉት ደ/ር አንዱዋለም አባተ፣ ከግሎባል ፒስ ባንክ ማሕበር ጋር ከምስረታው ጀምሮ ያላቸውን እውቂያ በመጥቀስ፣ ባላቸው የኪነ-ጥበብ፣ የፎክሎርና የስነ-ፅሁፍ ሙያ ከሀሳብ ባንኩ ጋር መስራት አገሪቷ የምትፈልግውን የሰላም አማራጭ ሁሉ ባላቸው ግዜና አቅም መስራታቸው እንደሚያስደስታቸው ገልፀው፣ ወደፊትም በማንኛው መንገድ ሰላምና የባንኩን የሰላም ሀሳቦች ለመደገፍ ፈቃደኛ ስለመሆናቸው ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ሌሎች ተቋማት፣ ግልሰቦች፣ ሚዲያና ሰላም ወዳዶች ሁሉ ሊተባበሩ እንደሚገባ በመድረኩ አንስተዋል፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ንግግር ያደረጎት ክቡር አንባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ለዘመናት የቆየው የግጭት ክስተት በሂደት እና በስራ የሚፈታ በመሆኑ፣ ግሎባል ፒስ ባንክ ይህንን ተገንዝቦ፣ ቅድሚያ ነጎረቤት በሚል የጀመረውን የሰላም ግንባታ ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ አክለውም፣ “ስልጣንን እና ጥቅማቸውን ለማቆየት ሲባል በኢትዮጲያ ውስጥ ሰላምን አያወኩ መቆየት፣ በሕዝብ መካከል ክፍፍል መፍጠር ጉልህ ችግር በሆነበት አውድ፣ እንዲህ አይነት ስልጠናና ውይይት መፍጠር ተገቢ በመሆኑ፣ በግዜ ልንጠቀመው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በጎረቤቶቻችን ሱዳን፣ ሶማልያ እና በአጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ የሚታዩ ግጭቶች ተዛምተው የሰላም ኡደቱን እየረበሹ በመሆኑ፣ የመረረውን ገፈት ከመቅመሳችን በፊት፣ በግዜ ሰላማዊ ንግግሮች፣ ውይይትና የሰላም ግንባታ ስራ መስራት ያስፈልጋል፣ ብለዋል፡፡ በሕዝብ መካከል ጥላቻና ፀብ የልም፤ ይህንን ፀብ የሚያራግቡትን ፖለቲከኞች በማስተማር ረገድ ሚዲያው ትልቅ ሚና ስላለው፣ ሚዲያው ሚናውን ለይቶ ለሰላም ሀሳብና ተግባራዊነቱ መቆም እንዳለበት፣ ለህብረተ-ሰቡም የሰላምን ዋጋ ማስረፅ እንደሚገባም ስታውቀዋል፡፡
ከተለያዩ ሚዲያ ለተውጣጡት ሰልጣኞች ስልጠናውን ያቀረቡት ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋዚጠኝነትና ስነ-ግባቦት ትምህርት ክፍል የተውጣጡ በጎ ፈቃደኛ መምህህራ፣ ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር በመተባበር ነው፡፡
2025-07-23