News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
ነሀሴ 8/2017 ዓ.ም.
#ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ
በግሎባል ፒስ ባንክ ሪፖርተር
ግልባለ ፒስ ባንክ ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ት/ቤት የመፅሐፍ ልገሳ አደረገ፡፡ ግምታቸው ሰላሳ ሺህ ብር ያላቸው 33 መፅሐፍትን በዋናው ግቢ ተገኝተው ያስረከቡት የገሎባለ ፒስ ባንክ ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው አየለ ሲሆኑ፣ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሶሻል ሳይንስ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ፕ/ሮ ዘለቀ አርፊጮ፣ የጋዜጠኝነት ት/ክፍል ሀላፊ አቶ እያዩ አለማየሁ እና የት/ክፍሉ መምህራን ተገኝተዋል፡፡
አቶ አርጋው አየለ በርክክቡ ወቅጥ እንዳሉት፣ “ይህ ድጋፍ ከዚህ በፊት በተፈረመው የመግባቢያ ውል መሰረት እርስበእርስ ለመደጋገፍ ቃል በተገባው መሰረት አንዱ ማሳያ ሲሆን፣ በአገር ውስጥ የታተሙ መፅፍትን ለአዲሱ ትውልድ ማስተዋወቅና እንዲህ ዓይነት አገር በቀል ዕውቀትን፣ ታሪክንና ሞራልን የሚያስተምሩ መፅሐፍት፣ ከአካዳሚያ ጎን ለጎን ቢነበቡ፣ በተለይም ለጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ተማሪዎችና ተመራማሪዎች ይጠቅማሉ፤” ብለዋል፡፡ የዚህ ዓይነቱ ድጋፍ በዚህ የሚገደብ ሳይሆን፣ ወደፊትም ቀጣይነት እንደሚኖረው ያነሱት ስራ አስኪያጁ፣ ከውጭ እና ከአገር ውስጥ ካሉ አጋሮች ለትምህርት ክፍሉ ጠቃሚ የሚሆኑ መፅሐፍትን በማስተባበር ለቤተ-መፅሐፍቱ ተጨማሪ ማጣቀሻዎችን እንደሚለግሱ ቃል ገብተዋል፡፡
የማሕበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ፕ/ር ዘለቀ አርፊጮ በበኩላቸው፣ ስለተደረገው ድጋፍ አመስግነው፣ “በኮሌጃችን ስር ለተቋቋመው አዲሱ የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ት/ክፍል ቤተ-መፅሐፍት ማደራጃና ማበልፀጊያ ከሚያግዙ ተግባራት መካከል ግልቦል ፒስ ባንክ ያደረገው ድጋፍ እንደጥሩ ምሳሌ የሚጠቀስና የሚያበረታታ ስለሆነ፣ ሌሎችም ይህንን አርዓያ በመከተል፣ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም፣ መፅሐፍቱ በበይዘታቸው፣ በሀሳብ አማራጭነታቸው ከተለያየ አመለካከትና ምንጭ ቢመጡም፣ መማሪያና ማጣቀሻ አገልግሎት ላይ የሚሰጡትቅምና የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ የድጋፍ ስራውን በትልቅ አድናቆት የምንመለከተው ነው፤” ብለዋል፡፡
“ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር የሚኖረን የመደጋገፍና አብሮ የመስራት ተግባራት የሚያበረታቱና እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ የምናደንቀው ነው፤” ያሉት የትምህረት ክፍሉ ኃላፊ አቶ እያዩ አለማየሁ፣ “ዛሬ የተደረገልን የመፅሐፍት ልገሳ ለተማሪዎቻችንና ለመምህራን የምርምር ስራና ለተጨማሪ እወቀት የሚረዱ በመሆናችው፣ ይህንን ስጦታ ከትምህርት ክፍሉ አንዱና ትልቁ ታሪክ አድርገን እንወስደዋልን፤” ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የርክክብ ስነ-ስርዓቱ በዋናው ግቢ፣ አዲሱ የት/ክፍሉ ቤተ-መፅሐፍት ውስጥ ተከናውኑ፣ ኩነቱ በጋራ የማስታወሻ ጎቶግራፍ መነሳት ተጠናቋል፡፡
2025-08-14