blog post

“ጥላቻችሁን_ወደ_ኤለክትሪክ_ሀይል_መቀየር_ቢቻል፤ አለምን_በሙሉ_ብርሃን_ማጎናጸፍ_ ይቻል_ነበር" ኒኮላስ ቴስላ የፓናል_ውይይት_በጥላቻ_ንግግር፣_በማህበራዊ

#ሀዋሳ፣ ኢትዮጵያ

ማስከረም 16/2018 ዓም. በሀዋሳ ኬር አውድ ኢነተርናሽናል ሆቴል፣ “ማህበራዊ ሚዲያና የጥላቻ ንግግርን” በተመለክተ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የጋዜጠኝነትና ተጋባቦት ት/ት ከፍል ከግሎባል ፒስ ባንክ ጋር በመተባበር በተካሄደው የፓናል ውይይት፣ ከአንጋፋው ዲፕሎማት ክቡር አምባሳደር ዲና፤ ከክቡር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እና ከግሎባል ፒስ ባንክ ሰራ አስኪያጅ ከአቶ አርጋው አየለ ጋር የመወያያ እና የሃሳብ መድረክ ተካሄደ፡፡

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ክቡር ዶ/ር ችሮታው አየለ መድረኩን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፤ የማህበራዊ ሳይንስና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን ፕ/ር ዘለቀ አርፊጮ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡ ከታዳሚዎች የተነሱት ሀሳቦች ደግሞ እጅግ አዋያይና አሰተማሪ ሆነው ውለዋል፡፡

በመድረኩ ቁልፍ ንግግር ያቀረቡት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰላምና የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል አንጋፋው ዲፕሎማት ክቡር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባደረጉት ገዢ ንግግራቸው  “ማህበራዊ ሚዲያውን ረብ ላለው ጉዳይ ብንጠቀምበት ብዙ ትሩፋቶች አሉት፤” ያሉ ሲሆን፣ ይህንን ለማደረግ ደግሞ፣ ሀሳብን በስልጡን መንገድ መለዋወጥ እና ጥላቻን በሃሳብ ማሸነፍ እንደሚገባ፡ የዶ/ር ኪንግን ዝነኛ ንግግር እማኝ አድርገው፤".....Hate cannot drive hate; only love can do that" ብለዋል፡፡

በመድረኩ_ ፓነሊስት_ የነበሩት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ክቡር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ “ዲጂታል ሚዲያውን እንዴት አድርገን ለሰላም ግንባታ እንጠቀመው” በሚል ሀሳብ የተለያዩ ጥናቶችን አጣቅሰው ሀሳባቸውን አራምደዋል፡፡ በዘለቄታዊነት ግን ማህበራዊ ሚዲያው ምህዳር ሰለሆነ ከጀርባው ያሉ ለሰላም እጦት ገፊ ጉዳዮች ላይ ማትኮር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

የግሎባል_ፒስ_ባንክ መሰራችና ሰራ አስኪያጁ አቶ አርጋው አየለ ደግሞ ለሰላማችን ችግር መፍሄ ያሉትን የሚመሩትን ደርጅት "የቅድሚያ ለጎረቤት" ፍልስፍናን አብራርተዋል፡፡ ሁላችንም "የየጎረቤቶቻችንን ሰላም፤ እምነት፤ ጾታ፤ ብሄር ሳንል፤ የቆዳ ቀለም ሳንለይ ብንጠብቅ ጥላቻን አሸንፈን ሰላም ማሰፍን እንችላለን፤" ያሉ ሲሆን፣ “በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታውስጥ ያለው ቀጥተኛ ችግር ከአንድ በላይ ያለን ማንነት ፍለጋ ነው፤ ይህም የበላይነትና የበታችነት ስሜት ችግር በመፍጠር፣ ያለንበትን ዘመን ውስብስብ ግንኙነት የተጋረጠበት አድርጎታል፤” ሲሉ ሞግተዋል፡፡

በእለቱ የፓናሊስት ዶ/ር መልሰው ደጀኔ (ተባ/ፕሮ) “ማህበራዊ ሚዲያው እና ዲጂታል ቴክኖሎጂው በዚህ የድህረ እውነት ዘመን ጥላቻን ለማራባት ምቹ ምህዳር መፍጠሩን የተለያዩ ጥናቶችን ዋቢ አድርገው አስረድተዋል፡፡ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለገነገነው ጥላቻ መፍትሄ ያልዋቸውን የአጭር እና የረዥም ጊዜ አማራጮችን አመላክተዋል፡፡

ጠማሕበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ፕ/ር ዘለቀ አርፍጮ በበኩላቸው “የጥላቻ ንግግር ማለት አንድን ማህበረሰብ፣ ቡድን ወይም ግለሰብን ዘርን፣ ብሔርን፣ ሐይማኖትን፣ ጾታን፣ አካል ጉዳተኝነትን እና ሌሎች የማንነት መገለጫ የሆኑትን በመጠቀም እንዲጠቃ፣ የሞራልና የስነ-ልቦና ጉዳት እንዲደርስበት ሆን ተብሎ የሚደረግ ትርክትና መልዕክት መሆኑንና ይህም በማህበረሰቡ መካከል አለመተማመን፣ ግጭት፣ ጦርነት እና ዘርፈ ብዙ ምስቅልቅሎችን የሚፈጥር መሆኑን አብራርተዋል።

በዚህ እጅግ ወቅታዊና አስፈላጊ የፓናል ውይይት መድረክ ላይ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቀድሞ ፕሬዚደንቶች፣ መምህራንና የሥራ ኃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ተወካዮች፣ ጋዜጠኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችና አንቂዎች እንዲሁም የወጣት ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

ዜናውን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!                                                                                                                                                                             https://www.youtube.com/watch?v=0n-_SrJyjHc

2025-09-27