News Single
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
Explore our peace-building initiatives and success stories on
achieving global peace through community unity on our Global Peace
Bank Blog.
እውቅናው የተሰጣቸው ለማህበረሰቡ በሚሰጡት ሰፊ ሰብዓዊ ድጋፍ፣ የህፃናት እንክብካቤ እና ለሰላም ግንባታ ለሚያበረክቱት የላቀ አስተዋፅኣ መኾኑ ተገልጿል። በተለይ በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰራ “ግሎባል ፒስ ባንክ” የተሰኘ የሀሳብ ባንክ አቋቁመው እየሰሩ መኾናቸው እውቅና ያሰጣቸው አድራጎት ነው።
አቶ አርጋው አየለ ላለፉት 20 ዓመታት የተጎዱ፣ የተጣሉ እና ድጋፍ ለሚሹ፣ ከ150 በላይ ለሚኾኑ ህፃናት ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ቢቆዩም ችግሩን በዘላቂነት መፍታት ባለመቻሉ ጎዳና ላይ የሚወድቁ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ ነው ይላሉ። በመኾኑም የችግሩ መንስኤ ናቸው የሚሏቸውን ግጭት፣ ፀብ እና ኹከት ለማረቅ ሲሉ በሰላም ግንባታ ሥራ ላይ መሳተፋቸውን አስታውቀዋል።
የተጀመረው ስራም ውጤታማ እንዲኾን ከሚዲያና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋራ እየሰሩ እንደኾነም አስረድተዋል። ከነዚህም ውስጥ እውቅና ከሰጣቸው ከአፍሪቃ ሬኔይሰንስ ቴሌቪዥን (ARTS) እና ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋራ የሶስትዪሽ ስምምነት ሰሞኑን መፈራረማቸውን አስታውሰዋል።
እውቅና የሰጣቸው የአፍሪካ ሬኔይሰንስ ቴሌቪዥን (ARTS) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል በላይነህ የአቶ አርጋው የሚመራቸው እህት ድርጅቶች ለማህበረሰቡ የሚሰጡት አገልግሎት፤ በተለይም ግሎባል ፒስ ባንክ በሰላም ገደንባታ ላይ እየሰራቸው ያለውን ስራ አድንቀዋል።
2025-12-05
